=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
አሏህ ሱ.ወ.ተ የሰው ልጆችን የፈጠረበትን አላማ ሲገልፅ በቁርአን እንዲህ ይላል:-
«የሰው ልጆችንም ሆነ ጅኖችን አልፈጠርኩዋቸውም እኔን ሊገዙኝ ቢሆን እንጂ።»
እኛ የሰው ልጆች የተፈጠርንበትን አላማ ረስተን አለማዊ በሆኑ ነገሮች ተነድፈን ፤ አሂራን ረስተን ዱንያን ለማሳመር ከታች ከላይ ማለታችነን ቀጥለናል። ይህ ምን ያህል ልቦቻችን በድንቁርና ፅልመት እንደተሸፈኑ የሚያመላክት ነው።
እስኪ በልቦቻችን ውስጥ ያለውን እውነታ በጥያቄ መልክ እንመልከት።
√ ቁርአንን በቀን ቢያንስ ሶስት ጊዜ የምንቀራ ምን ያህሎቻችነን?
√ ሶላታችነን በተደነገጉት የሶላት ሰዓት የምንሰግድ ፣ ኢስላማዊ እውቀትን ለመሻት የምንጣጣርስ ስንቶቻችን እንሆን?
√ ስለዲናችን ወቅታዊ ጉዳዮችስ ቁጭ ብለን የምንወያይ ስንቶቻችን እንሆን?
√ አይደለም ስለወቅታዊ ጉዳዮቻችን ቁጭ ብለን መወያየት ይቅርና ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ሰላምታን መለዋወጥ እረፍት እየሆነብን አይደለምን? እንደ ሙስሊምነታችን ከኛ የሚጠበቁብንን ነገሮች የምንሰራስ ስንቶቻችን እንሆን?
√ ወላጆቻችነን በቅን መንፈስ እያገለገልን ያለን ፣ ኢስላማዊ ባህሪያትን የተላበስን ፣ አሏህ ከከለከለው ነገር የተከለከልን ፣ የአሏህን ቅጣት ፈርተን ተውበት እያደረግን ስቅስቅ ብለን የምናለቅስ እና ሂወታችነን በቁርአንና በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሱና እየመራን ያለን ስንቶቻችን እንሆን?
إِنَّ الصَّلَاةَ تَنْهَى عَنِ الْفَحْشَاء وَالْمُنكَرِ
ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለች።
ሶላት ልብን ብርሃን የምታድርግ ፣ የስኬት ሚስጥር ፣ የጀነት ቁልፍና ከአሏህ ጋር ያለንን ትስስር የምናጠነክርበት ፣ የአሏህን ውዴታ የምናገኝበት ፣ ለአሏህ ትእዛዝ ያለንን ታዛዥነት ፣ ባርነታችንንና ለማኝነታችነን የምንገልፅባት ብቸኛዋ የኢባዳ ተግባር ናት። ሶላት በጭንቀት ጊዜ እረፍትን ሰጭ ፣ ለችግሮች መፍትሄና የሃጥያቶች ማበሻ ናት።
ዛሬ ዛሬ ሶላትን መስገድ ፣ ቁርአን መቅራት ፣ ሂጃብን መልበስ የትርፍ ጊዜ ስራ እየሆነ መጥቷል። በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ይህንን እውነታ ለማረጋገጥ በተለያዩ ማህበራዊ ድህረገፆች ፣ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና በየሰፈሮቻችን ባሉ መስጅዶች ያለውን አህዋል መመልከት በቂ ነው።
ሶላት አንዱ የኢስላም ምሰሶ እንደሆነ ይታወቃል። ሶላትን አለመስገድ አንዱን የኢስላም ምሰሶን እንደ መናድ ነው።
ለሶላታችን ትኩረት ልንሰጥ ይገባል። አትኩሮት አይደለም ለሶላት በውዱእ ወቅት እንኴ ትኩረት ሰጥተን ተረከዛችነን በደንብ እንድናጥብ ፣ እያንዳንዷን ክፍል እንድናዳርስና ተረከዛችንንም ከጀሃነም እሳት እንድንጠብቅ ከሁሉም ነገር በላይ ተወዳጅ የሆኑት ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) አዘውናል።
ጥራዝ 1,መጽሐፍ 3,የሐ.ቁጥር 57
አብዱሏህ ቢን አምር እንደተረከው
አንዴ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በጉዞ ወቅት ከኋላችን ቀርተው ነበር። ለሶላት ውዱእ እያደረግን እያለ ተቀላቀሉን። በእርጥብ እጃችነም እግሮቻችነን እያበስን ነበር። እናም ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሁለቴ እና ሶስቴ ተረከዛችሁን ከጀሃነም እሳት ጠብቁ አሉ።
• ቸልተኝነት
• ነገን እቶብታለሁ በማለት ሃጥያትን መዳፈር
• ከቁርአንና ከሐዲስ መራቅ
• ትኩረትን አለማዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ብቻ ማድረግ
• ማህበራዊ ድህረገፆችን አዘውትሮ መጠቀም
• መጥፎ ጓደኛ
• እውቀት አለመኖር
• የአሏህ ፍራቻ በልባችን ውስጥ አለመኖር
• የቀልብ መድረቅ
• በኢስላማዊ ባህሪ ተኮትኩቶ አለማደግ
• የአስተሳሰብ ዝንፈት
• ጌሞችን አዘውትሮ መመልከትና መጫዎት
• የሰይጣንን መንገድ መከተል
በሰላታችን ጠንካራ ለመሆን ከሶላታችን እንድንርቅ ያደረጉንን ነገሮች ልናስወግድ ይገባል።
۵ ዳእዋ ማድረግ
۵ ሰውየው በራሱ ከሶላት እንዲርቅ ያደረጉትን ነገሮች ነቅሶ እንዲያወጣ ማገዝ።
۵ ተውበት አድርጎ ወደ ሶላት እንዲመለስ ግፊት ማድረግ
-አብሮን እንዲሰግድ ማበረታታት
-ማስታወስ
- ለዚህ ሰው ሁሌም ከጎኑ በመሆን የሚቸግሩት ነገሮች ካሉ ማገዝ
۵ የአሏህ ፍራቻ በልባችን ውስጥ እንዲኖር ማድረግ
- የሶላትን ምንዳ ማስታወስ
- ሶላትን የመተው ቅጣት ምን እንደሆነና የፍርዱን ቀን መከራ ማስተንተን
- የዚች አለም ውስንነት በጥልቅ መረዳት
۵ እውቀትን መሻት
۵ ዱአንና ኢስቲግፋርን ማብዛት
۵ የመልካም ስብእና ባለቤት መሆን
۵ ከመጥፎ ጓደኛ መራቅ
۵ ታናናሽ ወንድሞቻችነን ፣ እህቶቻችንና ልጆቻችነን በኢስላማዊ ባህሪያት ኮትኩተን ማሳደግ
=> ከማንኛውም ነገር በላይ ለሶላት ቅድሚያ እንስጥ
'~'-.,__,.-'~'
_,.-'~''~'-.,_
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|